+251111265211 info@amharasc.org

News

የአማራ ምሁራን መማክርት የአሜሪካ መንግሥት ያወጣውን መግለጫ አወገዘ፡፡ መማክርቱ መግለጫውን ኢፍትሐዊ እና ሀገራዊ ሉዓላዊነትን የሚጥስ ሲል ገልጾታል፡፡

መማክርቱ በመግለጫው አሸባሪው ትህነግ በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ አካባቢዎች ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ሲያካሂድ እንደነበር ጠቅሷል፡፡  በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ጄ ብሊንከን ሰሞኑን የተሰጠው መግለጫ ኢፍትሐዊና በሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት እና ሉዓላዊነትን ያለመጣስ የተባበሩት መንግሥታት መርህን የሚቃረን ነው ብሏል፡፡… Continue reading

May 20, 2021 News

የስብሰባ ቀን መቀየሩን ስለማሳወቅ

ውድ የምሁራን መማክርት አባላት፡፡የምሁራን መማርት ጉባዔ በወቅታዊ ጉዳይ እና የምሁራን ሚና ዙሪያ ለመወያየት አመታዊ ስብሰባ ጠርቶ እንደነበር ይታወቃል ሆኖም ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት እና በሌሎች ተደራራቢ ፕሮግራሞች ምክንያት የምሁራን መማክርት አመታዊ ጉባዔ ከ16-17/2013 ዓ.ም ወደ ሚያዚያ 30- ግንቦት 1/2013 ዓ.ም የተቀየረ መሆኑን ከታላቅ ይቅርታ ጋር እናሳውቃለን፡፡… Continue reading

April 16, 2021 News

በኦሮሚያ ክልል በተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖች የቀጠለውን አማራ ተኮር የዘር ማጽዳት በተመለከተ ከአማራ ምሁራን መማክርት የተሰጠ መግለጫ።

“በኦሮሚያ ክልል በተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖች የቀጠለው አማራ ተኮር የዘር ማጽዳት በዓለም አቀፍ ወንጀል የሚያስጠይቅ ነው” የአማራ ምሁራን መማክርት። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና የፌደራል መንግስት በአማራ ሕዝብ ላይ በአማፂ ኃይሎችና በመንግሥት መዋቅር ውስጥ በመሸጉ የሽብር ተኮር ተግባር ተባባሪ አካላት የጋራ ቅንጅት እየተፈፀመ ያለውን አማራን የማጥፋት ዘመቻ በቁርጠኝነት ባለመከላከላቸው እና የዘር ማጽዳት ወንጀሉን በአደጋው ልክ ባለማውገዛቸው በኦሮሚያ … Continue reading

April 1, 2021 News

የስብሰባ ጥሪ ማስታወቂያ

የምሁራን መማክርት ጉባዔ 2ተኛ አመታዊ ስብሰባ ከሚያዚያ 16-17/2013 ዓ.ም በደብረብርሃን ከተማ በወቅታዊ ጉዳዮችና በምሁራን ሚና ላይ ውይይት ያካሂዳል፡፡ ስለሆነም በዚህ ስብሰባ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ የመማክርቱ አባላት እና ሌሎች ምሁራን በዚህ አድራሻ–› https://amharasc.org/conference-registration/ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን ፡፡ማሳሰቢያ፡- ተሳታፊዎች ወጫቸውን በራሳቸው የሚሸፍኑ ይሆናል፡፡… Continue reading

March 26, 2021 News

ምርጫው ፍትህዊና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን በተለያዩ ክልሎች የሚኖሩ የሌላ ብሔር ተወላጆች ውክልና የሚያረጋግጥ መሆን አለበት::

ምርጫ ዜጎች የአንድ ሀገር አካል መሆናቸው የሚገለጥበት አንዱ እና ዋነኛው ፖለቲካዊ ሂደት ነው፡፡ በሁሉን አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ (Universal Declaration of Human Rights) በአለም አቀፍ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶቸ ቃልኪዳን (International Covenant on Civil & Political Rights) እንዲሁም በአፍሪካ የሰዎች እና የሕዝቦች መብት ቻርተር (African Charter on Human & Peoples Rights) እንደተደነገገው በአንድ ሀገር ውስጥ … Continue reading

February 25, 2021 News

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የምሁራን መማክርት ጉባዔ አመታዊ የጠቅላላ ጉባዔ የአቋም መግለጫ

የምሁራን መማክርት ጉባዔ አመታዊ የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባውን ከህዳር 5-6ቀን 2013 ዓ/ም በአዲስ አበባ ያካሄደ ሲሆን የ2012 ዓመታዊ ሪፖርት እንዲሁም በ2013 ዕቅድ ላይ ተወያይ አጽድቋል። በተጨማሪም በወቅታዊ ሁኔታ ሰፊ ውይይት ያደረገ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የፖለቲካዊ አቋም ልዩነት ወደ ጎን በመተው ውስጣዊ አንድነትን በማጠናከር ሀገር እና ህዝብን በማዳን ትግል በጋራ መቆም እና ከሁሉም ሀገር ወዳድ ሀይሎች ጋር … Continue reading

November 17, 2020 News

የምሁራን መማክርት ጉባዔ አመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነዉ፡፡

ህዳር 5/2013 ዓ.ም የምሁራን መማክርት ጉባዔ አመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በአዲስ አበባ የተጀመረ ሲሆን፤ የክልሉ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኝሁ ተሻገር የአማራ ህዝብ እየገጠመው ያለውን ፈተና እና ይህንን ፈተና ለመሻገር ምሁራን እያበረከቱት ያለውን አስዋጽኦ አመስግነው፤ በቀጣይ የህዝባችንን ማህበራዊ፤ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት ሁላችንም በአንድነት መንቀሳቀስ እንዳለብን አሳስበዋል፡፡ መማክርቱ አመታዊ የተግባርና የፋይናንስ … Continue reading

November 15, 2020 News
  • 1
  • 2