+251111265211 info@amharasc.org

News

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የምሁራን መማክርት ጉባዔ አመታዊ የጠቅላላ ጉባዔ የአቋም መግለጫ

የምሁራን መማክርት ጉባዔ አመታዊ የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባውን ከህዳር 5-6ቀን 2013 ዓ/ም በአዲስ አበባ ያካሄደ ሲሆን የ2012 ዓመታዊ ሪፖርት እንዲሁም በ2013 ዕቅድ ላይ ተወያይ አጽድቋል። በተጨማሪም በወቅታዊ ሁኔታ ሰፊ ውይይት ያደረገ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የፖለቲካዊ አቋም ልዩነት ወደ ጎን በመተው ውስጣዊ አንድነትን በማጠናከር ሀገር እና ህዝብን በማዳን ትግል በጋራ መቆም እና ከሁሉም ሀገር ወዳድ ሀይሎች ጋር በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ በአጽንዖት በመረዳት እና በማመን የሚከተሉትን አቋሞች ወስዷል።
1. የሉዓላዊነታችን መገለጫ በሆነው በሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ላይ ኢትዮጵያ እና አማራ ጠል የሆነው አሸባሪው ትህነግ የፈጸመውን የሀገር ክህደት ወንጀል የምሁራን መማክርቱ በጽኑ ያወግዛል።
2. የፌደራል መንግስቱ በዚህ አሸባሪ ሃይል እየወሰደ ያለውን የሕግ ማስከበር ተግባር በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ አጥፊዎችን በህግ እንዲጠየቁ እንዲሁም ድርጅቱ በአሸባሪነት እንዲፈረጅ መማክርቱ ያሳስባል።
3. ትህነግ በሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ዳንሻ ላይ እና በአማራ ክልል ሕዝብ ላይ የፈፀመውን ጥቃት በማክሸፍ እና የትህነግን ወረራ በመቀልበስ ረገድ የአማራ ልዩ ሃይል እና ሚሊሻ ላደረገው ላቅ ያለ ጀብድ የተሞላበት ተጋድሎ የምሁራን መማክርቱ አድናቆቱን እና ምስጋናውን በአክብሮት ይገልጻል። የከፈላችሁት እኩሪ መስዋዕትነት ከትውልድ ትውልድ ሲታሰብ እንዲሁም በታሪክ ሲዘከር ይኖራል።
4. ኢሰብአዊነት የተጠናወተው አሸባሪው የትህነግ ህገ ወጥ ሰራዊትና ጀሌዎቹ ማይካድራና በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ በንጹሀን ዜጎች ላይ የፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲሁም ባህር ዳር እና ጎንደር የአውሮፕላን ጣቢያዎች የመንገደኞች ማረፊያዎችን (terminals)፣ ሌሎች የሲቪል ተቋማት እና የመኖሪያ ስፍራዎችን በተወንጫፊ ሮኬት በመምታት የፈጸመውን የጦር ወንጀል (war crime) የምሁራን መማክርቱ በፅኑ ያወግዛል። ይህ አሸባሪ ሃይል ጊዜ እና አቅም ከፈቀደለት ከዚህ የከፋ ኢሰብአዊ ድርጊት ለመፈጸም እና ቀጠናውን ለማወክ ወደ ኋላ የማይል በመሆኑ የፌዴራል መንግስት በዚህ ህገወጥ ሃይል እየወሰደ ያለውን የህግ የበላይነትን የማስከበር እርምጃ አለምአቀፉ ማህበረሰብ እንዲደግፍ የምሁራን መምክርቱ ጥሪውን ያስተላልፋል።
5. ትህነግ እና የትግራይ ሕዝብ አንድ እንዳለመሆናቸው መጠን በዚህ ወቅት በየትኛውም የሀገራችን ክፍሎች የሚኖሩ የትግራይ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ለምንም አይነት ያልተገባ ድርጊት እንዳይጋለጡ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እና የህብረተሰብ ክፍሎች አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርጉ የምሁራን መማክርቱ በአፅንዖት ያሳስባል።
6. በሌላ በኩል ትህነግ በስልጣን ዘመኑ ራሱን እንደገዥ መደብ አድርጎ የወሰደውን ቡድን እና ቤተሰቦቻቸው በዘረፋ የሀገራችንን ሀብት እንዲቀራመቱ ከማድረጉ ውጭ ቀሪውን ሰፊ የትግራይ ሕዝብ ለድህነት የዳረገ መሆኑ ለሰፊው የትግራይ ሕዝብ እና ምሁራን የተሰወረ አይደለም። ስለሆነም ሀገር ወዳዱ ሰፊው የትግራይ ሕዝብ እና ምሁራን ይህን አሸባሪ ሃይል መሸሸጊያ ባለመሆን አሳልፎ በመስጠት እንደጥንቱ ሀገራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ እና ውለታ እንዲውሉ የምሁራን መማክርቱ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል።


ክብርና ሞገስ ለተሰው ሰማዕታት!!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!!!
ህዳር 6/2013
አዲስ አበባ

November 17, 2020 News

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *