+251111265211 info@amharasc.org

News

የምሁራን መማክርት ጉባዔ አመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነዉ፡፡

ህዳር 5/2013 ዓ.ም የምሁራን መማክርት ጉባዔ አመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በአዲስ አበባ የተጀመረ ሲሆን፤ የክልሉ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኝሁ ተሻገር የአማራ ህዝብ እየገጠመው ያለውን ፈተና እና ይህንን ፈተና ለመሻገር ምሁራን እያበረከቱት ያለውን አስዋጽኦ አመስግነው፤ በቀጣይ የህዝባችንን ማህበራዊ፤ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት ሁላችንም በአንድነት መንቀሳቀስ እንዳለብን አሳስበዋል፡፡ መማክርቱ አመታዊ የተግባርና የፋይናንስ ሪፖርቱን አቅርቦ ያጸደቀ ሲሆን፤ የተጓደሉ የቦርድ አመራሮችን አስመርጧል፡፡ በዛሬው እለት የሃገራችን ወቅታዊ ተግዳሮት እና የምሁራን ሚና በሚል እንደ ኢትዮጲያና አማራ ምን ማድረግ እንዳለብን በጥልቀት ተወያይተናል፡፡ የተሳካና የጋራ መግባባት የተደረሰባቸው ነጥቦች ተለይተዋል፡፡ በአጭር፤ በመካከለኛና የረጅም ጊዜ ልንሰራቸው የሚገቡ ስትራቴጅካዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት አድርገነል፤ ወደተግባር እንደሚገባ ታምኖበታል፡፡ ስብሰባው በዛሬዉ እለትም ቀጥሏል፡፡

November 15, 2020 News

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *